You are currently viewing የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን አደነቁ በሚል የተሰራጨው መረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ነው
በፌስቡክ የተሰራጨው ቪድዮ (ፌስቡክ፣ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም)

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን አደነቁ በሚል የተሰራጨው መረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ነው

Fact checks / Video verification

AI-generated

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን አደነቁ በሚል የተሰራጨው መረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ነው

ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን አሞካሹ የሚለው ቪዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ነው። ይህ ጽሁፍ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ዶናልድ ትራምፕ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን የአመራር ብቃት አድንቀው የሰጡት ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ ወይም ማስረጃ ማግኘት አልተቻለም።

Share fact-check Telegram Facebook WhatsApp X

AI-generated

251-check ኦንላይን የሚገኙ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም ባደረገው የማጣራት ስራ ቪድዮው ከ80% በላይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

Still from a Facebook video showing Prime Minister Abiy Ahmed and US President Donald Trump with the caption "Trump about Abiy Ahmed"
በፌስቡክ የተሰራጨው ቪድዮ (ፌስቡክ፣ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም)

The claim

Claim being checked

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጠንካራ እና ባለራዕይ መሪ”

ፌስቡክ፣ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም / ዋናውን ቪድዮ ይመልከቱ

በመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም “ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጠንካራ እና ባለራዕይ መሪ” የሚል የመግለጫ ጽሁፍን በማያያዝ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተናገሩት በሚል ጽሁፍ፣ ከ39 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገጽ አንድ ቪድዮ አሰራጭቶ ነበር።

ይሁን እንጂ 251-check የተሰራጨውን መረጃ መርምሮ ቪድዮው በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን በማረጋገጥ የተቀናበረ ብሎታል።

The evidence

251-check የትራምፕን ንግግሮች ከዚህ ቀደም ይፋ ከተደረጉ የመዝገብ ሰነዶች እና ሚዲያዎች ጋር በማነጻጸር ባደረገው ፍተሻ ዶናልድ ትራምፕ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አመራርነት በግል የሰጡት ምንም አይነት ይፋዊ ምስክርነት አለመኖሩን አረጋግጧል።

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዋናነት ስለ ኢትዮጵያ የሚያደርጓቸው ንግግሮች አብዛኞቹ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በአባይ ወንዝ ዙሪያ ያተኮሩ ናቸው። በሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው በተለይም በፈረንጆቹ 2026 በተካሄዱ እንደ ዳቮስ ፣ G-7 ጉባኤ እና በኒውዮርክ ሲራኩስ ባደረጓቸው ንግግሮች፣ ኢትዮጵያ በገነባችው ግዙፍ ግድብ ምክንያት የአባይን ውሃ በብቸኝነት በመውሰዷ ለግብፅ ትልቅ ስጋት መፍጠሯን በተደጋጋሚ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ግድቡ “በአሜሪካ ገንዘብ የተገነባ ነው” በማለት የቀድሞ የአሜሪካ አስተዳደሮችን ሲተቹ ቆይተዋል፤ ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ግድቡ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ሀብት የተገነባ መሆኑን በመግለጽ ይህንን አባባል በተደጋጋሚ ውድቅ አድርጎታል።

ትራምፕ ይህንን ጉዳይ “አደገኛ እና ትልቅ ችግር” ሲሉ በመጥራት ፣ ኢትዮጵያን ፣ ግብፅን እና ሱዳንን ዳግም ወደ ድርድር በማምጣት አሜሪካ ዘላቂ ስምምነት እንዲደረስ የማደራደር ፍላጎት እንዳላት አስታውቀዋል።

ከሕዳሴ ግድብ ባሻገር የፕሬዝደንት ትራምፕ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ ሌሎች ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎችንም አሳልፏል። በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም ለአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት እና የውጭ ፖሊሲ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረጥ ነፃ የንግድ ዕድል (AGOA) ውጪ ሆና እንድትቆይ የብሔራዊ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አራዝመዋል። በተጨማሪም በአሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ የመኖሪያ እና የሥራ ፈቃድ (TPS) እንዲቋረጥ አስተዳደራቸው ውሳኔ ማሳለፉ በንግግሮቻቸው እና በመግለጫዎቻቸው ውስጥ በዋናነት የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።

251-check ኦንላይን የሚገኙ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም ባደረገው የማጣራት ስራ ቪድዮው ከ80% በላይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል። ከዚህም በላይ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ እና ያልተለመዱ አይነት እንቅስቃሴዎችን ከዚህም ባለፈ ተከታታይ ያለ ትንፋሽ መቆራረጥ የተነገሩ ንግግሮችን ማየት ተችሏል።

AI-detection result rating the Trump–Abiy video 88% likely AI-generated, classified as synthetic
ምስል 1. የቪድዮው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርመራ ውጤት፦ 88% በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ (Synthetic)።

በተጨማሪም በቪድዮው ጥቅም ላይ የዋለውን ድምጽ ትክክለኛነት ለማጣራት በተደረገው ጥረት አንድን ድምጽ ምን ያህል የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንደተጠቀመ ለማጣራት በተዘጋጁ መሳሪያዎች የተደረገው ምርመራ ድምጹ 100% በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረከ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።

AI voice-detection result rating the audio of the Trump–Abiy video 100% AI-generated
ምስል 2. የድምጹ ምርመራ ውጤት፦ 100% በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረከ ድምጽ።

Why it matters

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ቪድዮዎች የዓለም መሪዎች ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ። እንዲህ አይነት ቪድዮዎችን ከማጋራታችን በፊት መረጃውን ከታማኝ የዜና ምንጮች ወይም ከመሪዎቹ ይፋዊ ገጾች ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

Conclusion

ይህ ጽሁፍ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ዶናልድ ትራምፕ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን የአመራር ብቃት አድንቀው የሰጡት ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ ወይም ማስረጃ ማግኘት አልተቻለም።

ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች 251-check ተንቀሳቃሽ ምስሉ የተቀናበረ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

Sources

  1. Facebook reel (the claim) → facebook.com
  2. Addis Standard, Trump revives GERD criticism at G7 → facebook.com/AddisstandardEng
  3. Egypt Today, Trump on the dam’s financing → facebook.com/EgyptTodayMag
  4. DW Amharic → dw.com
  5. Ethiopian Policy, AGOA sanctions extended → ethiopianpolicy.com
  6. BBC, TPS decision → bbc.com

Corrections

No corrections have been made to this article. Spotted an error? Request a correction.

Leave a Reply